Tenes @henok__berhanu New Music
https://youtu.be/9qvLJfkCPgM
ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራ እና ተከብራ ለዘላለም ትኑር ????????❤️
@wub_alem_family
@abolmultimedia
@mela_productions
@mela_muziqa
.
.
Ethiopia will prevails
ተነስ
ተነስ ተነስ ተነስ ተነስ ተነስ ተነስ
እኔስ ምን አደረኩላት ለሃገሬ ለኢትዮጵያ
በማንም ማልተካት የለሌላት አምሳያ
ሲነኩሽ እያየሁ ሊያጠፋሽ ከምድር
ታላቋን ሃገሬን ሊያደርጉብኝ መንደር
መሰሪ ነው ልቡ ካልበላሁ አትብላ
መበለጥ የማይወድ የጅብ ሆድ ጎተራ
ከነ ግሳንግስህ አብልታ አጠጥታ
እንዴት ካልነከስኩ አልክ የእናትክን ውለታ
መኖርን እየቻልክ ይቅር በሉኝ ፍቅር
ጭራሽ ጉድጏድ ቆፈርክ ሀገሬን ልትቀብር
በል በቆፈርከው ውስጥ አንተው ሂድ ግባበት
ከኛ ጭቃ የለም ልባችን ነው የአለት
በል ጀምረሃል ለኩስለት እሳት
ገሀነም ስትመኝ ላይቀር ልትገባበት
በል ተዘጋጅ ጏዴ ጉዞ ነው ወደላይ
በሚስትና በሀገር ማን ሲቀልድ ልታይ
አሳዶ ይግረፍህ የአንተው ሴራ ጅራፍ
ሀገሬ እንድትደርስ ከልማቷ ደጃፍ
እምቢ ካለ በቃ አባረህ ገረፈው
ከሃገር ማን ይበልጣል ስትኖር ነው ምትኖረው
ካልጋጥኩህ ልሙት ሲል ከመርዝ ላይ ቀድቶ
ስተወው ሚይዝህ ደግሞ ስትሄድ ፈርቶ
እንደው ሲፈርድብሽ አለቅ ሚል እድፍሽ
አንዱ ሲወድቅ ላንቺ ሌላው ሲዝትብሽ
ጥልቅ ነሽ ሚስጥር ነሽ ይብላኝ ላላወቀሽ
ዛሬም ልጆች አሉሽ ፊትሽ ሚወድቁልሽ
ምንስ በድለሽ ነው እንዲህ የጨከኑብሽ
በስጋሽ ደልበው ያልካሱት ላጥንትሽ
ይኸው ትንሽ ትልቅ ገበሬው ሚሊሻው
እርሱም አልበቃ ሲል ከፈረስ እስከ ውሻ
እንዲያ ሲዘምቱብሽ በጫካው በጢሻ
ምን ግን ቢያቀምሱት ነው ሊያጠፉሽ የሚሻ
የዓሉላ አባ ነጋ የዮሃንስ ሀገር
ምን አረም በቀለ ከጀግኖቹ መንደር
በያሬድ ዝማሬ ሲነቃ እንዳልነበር
ይኸው በቦምብ ዛሬ መቅደስ ያፈርስ ጀመር
ስማ ወጣት ከሆንክ ተማር ከሄርሜላ
ለቀረው ትውልድህ አበጅላት መላ
ኋላ እንዳይቆጭህ ያጣህለት ከለላ
ቁርጥ ያለ ከሆንክ የኋላ የኋላ
ወዳጅም ጠላትም ከሩቅ ተመልክቶ
በንካ ሰላምታ በአጉል እቶ ፈንቶ
አብሮ የበላውን ስንቱን ነገር ረስቶ
ማሰብ ተስኖታል አጉልቶ አስፍቶ
አስፍቶ አስፍቶ
ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ
ለዘላለም ትኑር።
#ethiopiaprevails #nomore
#addisababa #asmera #ethiopia #eritrea
#eastafrica #african #proudethiopian
#ethiopianmusic
#hiphop #habesha
ከወሎሰፈርእስከdc