❤️ ሰብስክራይብ በማድረግ የዚህ ድንቅ ቤተሰብ አባል ይሁኑ።
???? ምርጥ ምርጥ የአማርኛ የዘፈን ግጥሞችን እና ሙሉ አልበሞችን እያዘጋጀን እናቀርባለን።
???? ላይክ እና ኮሜንት እና ሼር በማድረግ ድጋፍዎን ያሳዩን….. እናመሰግናለን ።
???????????? ???????????? ????????????
አርማሽ ይውለብለብ ከደጄ
ልቤ ናፍቆሻል ወዳጄ
እኔስ እስካይሽ ጨነቀኝ
ሀገሬ መምጫሽ ናፈቀኝ
ቀን እየሄደ ቀን መጣ
ልቤ ከሃሳብ ሳይወጣ
መጥታ ታብሰው እንባዬን
ሀገሬን ጥሯት አርማዬን
መቼም ከዚህ ምድር ላይ
ሄዶ ነው ሁሉም ቀሪ
ሃገር ናት ቋሚ ሰንደቅ ቂ
ለዘላለም ኗሪ
ትንላንትም እንደጀንበር
እያዩት ካይን ይርቃል
ኢትዩጵያ እንድትመጪ
ስንት ቀን ይበቃል
እኔማ ላይሽ በቶሎ ምኞት ነበረኝ
ግን ባባሁ ናፈኩሽና እንባ ቀደመኝ
እኔማ አለሁ እስካሁን ተስፋ ሰንቄ
በወንዜ ባገሬ እያለሁ አገር ናፍቄ
ወተሽ በምስራቅ አንቺ ያለም ጀንበር
አንድ አርጊን እና ጠላትሽ ይፈር
የቦረቅኩበት በልጅነቴ
የያኔው መልክሽ ብቅ ሲል ፊቴ
እየመለሰኝ ወደ ትላንቱ
ናፍቆኝ በብርቱ ትዝ አለኝ የጥንቱ
አርማሽ ይውለብለብ ከደጄ
ልቤ ናፍቆሻል ወዳጄ
እኔስ እስካይሽ ጨነቀኝ
ሀገሬ መምጫሽ ናፈቀኝ
ሀገር ለክብሩ ሲጣራ
ከፍ ያደረግነው ባንዲራ
ዘመም ሳይል ቀን ጎሎ
ባክሽ ኢትዮጵያ ነይ ቶሎ
ብዙ ነሽ አንቺ ሃገሬ የሞላሽ ታምራት
ምኩራብብሽ የተፈራ የነፃነት ቤት
የአርበኞች የድል ችቦ ለትውልድ እንዳበራ
መኖር ላገር ሲሆን ሞትም አያስፈራ
እኔማ ላይሽ በቶሎ ምኞት ነበረኝ
ግን ባባሁ ናፈኩሽና እንባ ቀደመኝ
እኔማ አለሁ እስካሁን ተስፋ ሰንቄ
በወንዜ ባገሬ እያለሁ አገር ናፍቄ
ዓመት አውዳመት ድገመን ሲሉ
ልጆች በቀዬው ችቦ እያበሩ
መስቀል ፋሲካው ዒድ እንቁጣጣሽ
አውዳመት አይሆን አንቺ ካልመጣሽ
ዘመን አድሰሽ በፍቅር ቀለም
ብቅ በይ ኢትዮጵያ ሁኚና መስከረም
ሆነሽ መስከረም.......አሲዮ
ብቅ በይና.....ቤሌማ
እንበል አሲዮ.......አሲዮ
ናና ቤሌማ....ቤሌማ
ብቅ በይና.....አሲዮ
ሆነሽ ሙሽራ.....ቤሌማ
ይብቃን ስደቱ.......አሲዮ
ስቃይ መከራ.....ቤሌማ
ቤሌም ቤሌማ...አሲዮ
ናና ቤሌማ...ቤሌማ
ዘር ያበቀለው...አሲዮ
ታጭዷል መከራው...ቤሌማ
የኢትዮጵያዊነት...አሲዮ
አሁን ነው ተራው...ቤሌማ
አሲዮ.......አሲዮ
ናና ቤሌማ....ቤሌማ
ዘመን አድሰሽ... አሲዮ
በፍቅር ቀለም... ቤሌማ
ብቅ በይ ኢትዮጵያ... አሲዮ
ሆነሽ መስከረም...ቤሌማ
እኛስ ከመንገድ ላይ ጠፍተን መቼ አወቅነው
ብንሄድ ብንሄድ አንደርስም ገና ነው
በመባረኪያችን ከመንገድ ላይ ዝለን
አይበቃም ወይ ማሳል በዘር ጉንፋን ታመን
በዘር ጉንፋን ታመን
ቀን አለ በሉ
ቀን አለ ገና
አለ በሉ
ቀን አለ ገና
ለኢትዮጵያዊነት ቀን አለው ገና
ስንሽን በክፉ ያነሳሽ ጠፍቶ
አርማሽ ከፍ ሲል ሰማይ ላይ ወጥቶ
እኛ ልጆችሽ ልናይ ቆመናል
አንድ ቀን መጥቶ አንድ ያደርገናል
ቀን አለ በሉ
ቀን አለው ገና (*2)
ስንቱ ተሰደደ ይብቃን ሀዘን ለቅሶ
አንድ ሆነሽ ኢትዮጵያ ባየን ፍቅር ነግሶ
ዘር ያበቀለው ታጭዷል መከራው
የኢትዮጵያዊነት አሁን ነው ተራው
ቀና በል አሁን
ቀና በል ቀና (*2)
የጀግኖቹ ልጅ አንተ ነህና
ካገር ወዲያ ሞት ሞት የለምና
ዝም ያለ መስሎ ኢትዮጵያዊነት
ማንም አይገታው የተነሳለት
ቀና በል አሁን
ቀና በል ቀና
ጥንት አባቶችህ ያቆዩትን
ከፍ አርገህ ይዘህ ባንዲራህን
ቀና በል አሁን
ቀና በል ቀና